Russian House in Addis Ababa / Русский дом в Аддис-Абебе

@rcscethiopia · education · English · active

Subscribers 4.5K Subscribers, last 30 days: 4.5K → 4.5K +0 24h
Reach per post (ERR) 20.7%938 avg views
Posting 2.4/day last 1 day ago
Reactions per 1K views 10.9 👍 ❤ 🔥
repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹

ዛሬ የመደመር መጽሐፍ ወደ ሩሲያኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለንባብ በቅቷል። በተዘጋጀው የመጽሐፉ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ በአካል ተገኝቼ በመካፈሌም ታላቅ ደስታና ኩራት ተሰምቶኛል። ይህ ታሪካዊ ስኬት የመደመር ፍልስፍና ከኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ተነስቶ ዛሬ ላይ ድንበር በመሻገር ወደ መላው ዓለም እየሰፋ መሄዱን የሚያሳይ ህያው ማረጋገጫ ነው። ከዚህ በፊት መጽሐፉ ከአገር ውስጥ ቋንቋዎች በተጨማሪ በእንግሊዝኛ፣ በቻይንኛ እና በአረብኛ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ለብዙኃን አንባቢያን መድረሱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ሀሳብ ድንበር ተሻግሮ በሰፊው የሩሲያኛ ተናጋሪ ደጃፍ መድረሱ የፍልስፍናውን ዓለም አቀፋዊ ተደራሽነትና ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ ይበልጥ ያጎለብተዋል። ይህ እርምጃ የመደመርን ፍልስፍና፣ እሴቶችና ሀሳቦች ከኢትዮጵያ አልፈው ለሌሎች ሕዝቦች የሚደርሱበትን አዲስ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም የምታበረክተው የራሷ የበሰለ ሀሳብ እንዳላት በተግባር የሚያሳይ ነው። ሩሲያ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የሥነ ጽሑፍና የዕውቀት መማሪያ ምድር ሆና እንዳገለገለች ሁሉ፣ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ሀሳብ በሩሲያኛ ቋንቋ ለሩሲያ አንባቢያን መድረሱ የዕውቀት ልውውጡን ሙሉ ያደርገዋል። ለዚህ ስኬት መሳካትና ለመጽሐፉ ዝግጅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን የሩሲያ ቱዴይ (RT) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና አመራሮች ያደረጉትን ጥረትና ትጋት በከፍተኛ ደረጃ አደንቃለሁ። ይህ አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የበለጸጉ አገር በቀል እውቀቶች፣ ባህሎችና ፍልስፍናዎች በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ይበልጥ ለማስተዋወቅና በሕዝቦች መካከል ጠንካራ የባህልና የሃሳብ ድልድይ ለመገንባት የሚኖረው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው።

Views over time

02505007501K29 Oct 12:0411 Nov 02:4682729 Oct 12:04: 0 views11 Nov 02:46: 827 views
Snapshots we took after posting.
WhenViews
29 Oct 2026, 12:040
11 Nov 2026, 02:46827

Who shared this post

Posts in other channels we index that link to this one. (Forwards with a hidden source can't be traced.)

Nobody yet.