Russian House in Addis Ababa / Русский дом в Аддис-Абебе

@rcscethiopia · education · English · active

Subscribers 4.5K Subscribers, last 30 days: 4.5K → 4.5K +0 24h
Reach per post (ERR) 20.7%938 avg views
Posting 2.4/day last 1 day ago
Reactions per 1K views 10.9 👍 ❤ 🔥
repost from ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቃውንት በሩሲያ ትምህርት ቤቶች መማራቸው በጣም ከፍተኛ ጠቀሜታ ነበረው – መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል 🌟 ሊቃውንቱ ቤተ ክርስቲያንን በጥሩ ሁኔታ ያገለግላሉ፤ ሁሉም በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 🗣 “በነገረ-መለኮት የዶክትሬት (ፒኤችዲ) ደረጃ ከፍተኛ ትምህርት አግኝተው ተመልሰዋል፤ በቤተ ክርስቲያኗም በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ ያገለግላሉ። ስለዚህ ስለ ሩሲያ ትክክለኛ እውቀት እንዲኖረን በጣም ጥሩ አገናኝ (ድልድይ) ሆነዋል፤ በእነዚህ ሰዎች አማካኝነት የተሳሳተ ወይም የተበላሸ እውቀት አይኖረንም።” ብለዋል፡፡ 👉 የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው “ለመላ ዓለም ሰላም” የተሰኘ የፎቶ ዐውደ–ርዕይ በአዲስ አበባ ለዕይታ ክፍት ሆኗል፡፡ 📹 መምህር ዳንኤል፣ "የሩሲያ የመንፈሳዊ ባሕል ቀናት በኢትዮጵያ" መርሃ-ግብር ወቅት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ልዑካን መካከል ከተደረገው የፓናል ውይይት ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ የነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች በቪዲዮው ይመልከቱ። ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X

Views over time

05001K23 Sep 16:3811 Nov 02:461K23 Sep 16:38: 0 views11 Nov 02:46: 1,000 views
Snapshots we took after posting.
WhenViews
23 Sep 2026, 16:380
11 Nov 2026, 02:461K

Who shared this post

Posts in other channels we index that link to this one. (Forwards with a hidden source can't be traced.)

Nobody yet.