✔️የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የዓለም አቀፍ የሕፃናት ድርጅቶች ማህበር (International Association of Children's Organizations- IACO) በአባልነት ሊቀላቀል ነው። የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ልዑክ ቡድን በሩስያ የዓለም ወጣቶችና ሕፃናት ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ይፋዊ የልዑክ ቡድኑ በሩስያ ፌዴሬሽን የካተሪንበርግ (Yekaterinburg) ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫል እና ከፌስቲቫሉ ጎን ለጎን በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የሕፃናት ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። በልዑክ ቡድኑ የምክር ቤቱ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁነኝ መሐመድ እና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ መሐመድ ማህሙድ ተካተዋል። በዓለም አቀፍ የወጣቶች ፌስቲቫሉ ላይ ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በግላቸው ተመዝግበው በፌስቲቫሉ አዘጋጅ ኮሚቴ የተመረጡ ወጣቶችና ሕፃናት በሰፊው እየተሳተፉ ነው። ከተሳታፊዎቹ መካከል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች፣ ወጣት ተፅዕኖ ፈጣሪዎች (Influencers)፣ እና ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ። በፌስቲቫሉ ቀጣይ ቀናት የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት የዓለም አቀፍ የሕፃናት ድርጅቶች ማህበር (International Association of Children's Organizations – IACO) ይፋዊ አባል እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህም ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ሕፃናት በዓለም አቀፍ መድረኮች ተሳትፎን ለማጠናከር፣ አዳዲስ የትብብር እድሎችን ለመፍጠር እና የወጣቶች ዲፕሎማሲን ለማጎልበት ጠቃሚ ምዕራፍ እንደሚሆን ይገመታል። ከፌስቲቫሉ ጎን ለጎንም የልዑክ ቡድኑ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ አጋር ተቋማት፣ ከተለያዩ አገራት የወጣት ሚኒስትሮችና የወጣቶችና የሕፃናት ድርጅቶች ጋር ዘላቂና ስትራቴጂካዊ አጋርነቶችን ለመገንባት የሚያስችሉ ውይይቶችን፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን እና የትብብር ምክክሮችን እያካሄደ ይገኛል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት በመሰል ዓለም አቀፍ መድረኮች የኢትዮጵያን ወጣቶችን ድምፅ በብቃት በማሰማት፣ የወጣቶች ዲፕሎማሲን በማጠናከር እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር የትብብር አድማሱን በማስፋት ተልዕኮውን በቁርጠኝነት እየተወጣ ይገኛል። የኢ/ወ/ም/ቤት 🔼ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን 🔼 🌐 የማህበራዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ! 🎁BOOST❤️Telegram📖Facebook🐦(X)😀LinkedI